የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ድንግል ሆይ ስለአንቺ

Lyrics

ድንግል ሆይ ስለአንቺ ነውና መሐሪ

አማልጅኝ ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ

ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ

ፊቱንም እንዳላይ ሥራዬ አሳፈረኝ

ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ

ትእዛዙን እንደሻርኩ ሕጉን እንደጣስኩኝ

በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ

እለምነዋለሁ ከአሁኑ ይቅርታ

አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሣሪ

አማልደኝ ከጌታ ከፈጣሪ

ጻድቃን ሰማዕታት እናንተ ሁላችሁ

አማልዱኝ ከአምላኬ ከአምላካችሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening