የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ድንግል ሆይ ስላንቺ

Lyrics

ድንግል ሆይ ስላንቺ ነውና መሐሪ

አማልጂኝ ከአንዱ ልጅሽ ከፈጣሪ } /2/

ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ

ፊቱንም እንዳላይ ስራዬ አሳፈረኝ

ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ

አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሣሪ

አማልደኝ ከጌታዬ ከፈጣሪ

በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ

እለምነዋለሁ ከአሁኑ ይቅርታ

ጻድቃን ሰማዕታት እናንተ ሁላችሁ

አማልዱኝ ከጌታዬ ከአምላካችሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening