የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ዕዳ አለብን

Lyrics

የእመቤታችን አማላጅነቷን

ክብሯን የቀነስን ያዋረድን ዕዳ አለብን /2/ ከፈጣሪያችን /2/

የተሰጣት ሙሉ ሥልጣን ክብርን ያገኘች በቃል ኪዳን

ስሟን የጠራ እንደሚድን በመጽሐፍ ሲነግረን

ቤዛዊተ ኩሉ የተባለች

በእነ ቅዱስ ኤፍሬም የተመሰገነች

በእነ አባ ጊዮርጊስ ውዳሴን ያገኘች

በመናፍቃን ዘንድ ምነው ተዘነጋች

ከሴቶች ሁሉ ልዩ ናት እያልን

በሁለቱም ወገን በፍፁም ድንግል

የብርሃን እናቱ ማርያም ስትባል

በደካሞች ዘንድ እንዴት ትቃለል

ቃና ዘገሊላ ከልጇ ጋር ሳለች

ከሠርግ ቤት ገብታ ድንግል አማልዳለች

እንኳንስ እመ አምላክ ቤዛዊተ ኲሉ

ጻድቃን ሰማዕታት በእውነት ያማልዳሉ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening