✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ምስጋና ለስምሽ
Lyrics
ምስጋና ለስምሽ ድንግል እመቤቴ
በአንቺ አማላጅነት ድኅነት በማግኘቴ
ቅዱሳን አባቶች ቀንም ከሌሊት
ለአንቺ ይቀኛሉ እንዲህ በማለት
ከሀገረ ብህንሳ ፍቅርሽ አስገድዶት
የአንቺ ንጽሕና ፍፁም አስደንቆት
አባ ሕርያቆስ ተሞልቶ በመንፈስ
ድንግል ሆይ አለ አንቺን ለማወደስ
ፋራን የተሰኘሽ የዕንባቆም ተራራ
በረከት የሞላሽ የገነት አዝመራ
ዕፀ ጳጦስ የተባልሽ የሙሴ ጽላት
የይስሐቅ መዓዛ የአብርሃም ደግነት
እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ
በቀኝ ትቆማለች አምራ ንግሥቲቱ
ባለገንዘቦችም አሕዛብ በሙሉ
ለክብርሽ ዝቅ ብለው ለአንቺ ይሰግዳሉ
ዓለም የዳነብሽ አንቺ የኖኅ መርከብ
ምስጋናሽ መብዛቱ እንደሰማይ ኮከብ
ዘወትር ሁልጊዜ ቢሰላ ቢወራ
ድንግል ሆይ አያልቅም አንቺ ድንቅ ስራ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.