የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

እዘኝልን

Lyrics

እዘኝልን ድንግል የአምላክ መንበር

ዓለሙን በማየት ወድቀን እንዳነቀር /2/

በኃጢአት በበደል ከልጅሽ ለራቅን

በዝሙት በሀሜት ዛሬም ለወደቅን

በዲያብሎስ ተንኮል ለተተበተብን

በአማላጅነትሽ ዛሬም ተማፀኚ

ከኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረትን ለምኚ /2/

በንስሐ ታጥበን በፍቅሩ ተስበን

ከልጅሽ እግር ስር ለመቀመጥ አብቂኝ /2/

በፈፀምነው በደል ተፀፃች አድርጊን

መራራ እንባ እናፍስ ልብን መልሽልን/2/

ፈቃደ ሥጋና ፈቃደ ሰይጣን

ዓለም ተደርባ ስታስጨንቀን /3/

ሰላምን ተጠምተን ስንንከራተት

ድንግል ድረሽልን የአምላክ እናት /2/

እባክሽ አትለይን እስከመጨረሻው

እየቀረበ ነው ክርስቶስ መምጫው /2/

ድንግል ማርያም ሆይ እባክሽ አሳስቢ

ለጻድቃን አይደለም ለኃጥኣን ብለሽ /2/

በቀኝ እንዲያቆመን በዳግም ምጽአቱ

ድንግል ለምኝልን ለአምላክ እናቱ

ድንግል ለምኝልን ለአምላክ ወላዲቱ

ቡሩካን ልጆቼ ብሎ እንዲቀበለን

ፍቅሩን ቸርነቱን አስቦ እንዲምረን /3/

ድንግል አደራሽን ስለኛ አሳስቢልን

በእርሱ መሰረት ላይ ክርስቶስ ያቁመን/2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening