✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
የአማኑኤል እናት
Lyrics
የአማኑኤል እናት ጸለየች ኢትዮጵያን አድናት
ጌታ ሆይ አድናት እያለች
የጌታዬ እናት ጸለየች ኢትዮጵያን አድናት
ጌታ ሆይ አድናት እያለች
የምወደው ህዝቤ አሥራት የሰጠኸኝ
በረሃብ በእርዛት ምነው ተጎዳብኝ
የፍቅር ረሃብ የሰላም ጥማቱ
ምነው መንገላታት ምነው መዋተቱ
ሆና ተሰርታለች መንፈሳዊት በአት
ድንግል አሥራቷ ቃል የተገባላት
ሐሰቱ ቅጥፈቱ ስለማይስማማት
ከእንግዲህ ወገኔ መመለስ አለበት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.