✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ሰላም ላንቺ ይሁን
Lyrics
ሰላም ላንቺ ይሁን /3/ ማርም ድንግል /2/
የሴቶች መመኪያ የሴቶች አክሊል /2/
የሴቶች መመኪያ የሴቶች /2/ የሴቶች አክሊል
ሰላም ላንቺ ይሁን /3/ የሁሉ እመቤት /2/
የኃጥኣን ተስፋ የጻድቃን ሕይወት /2/
የኃጥኣን ተስፋ የጻድቃን /2/ ሕይወት
ሰላም ላንቺ ይሁን /3/ የሁሉ ወዳጅ /2/
የጽድቅ መሰላል የዓለም አማላጅ /2/
የጽድቅ መሰላል የዓለም /2/ አማላጅ
ሰላም ለወለድሽው /3/ አምላካችንን /2/
ሰማይና ምድር የማይችሉትን /2/
ሰማይና ምድር የማይችሉት የማይችሉትን
ሰላም ለእመቤቴ /3/ አምላክን ለወለድሽ /2/
የሰማይ መላእክት የሚያመሰግኑሽ /2/
የሰማይ መላእክት /2/ የሚያመሰግኑሽ
ሰላም ለእመቤቴ /3/ አምላክ ለመረጠሽ /2/
ከሴቶቹ ሁሉ የተባረክሽ ነሽ /2/
ከሴቶቹ ሁሉ የተባረክሽ /2/ ነሽ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.