የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

የእኛ እመቤት

Lyrics

ነይ ነይ የእኛ እመቤት ነይ ነይ

የዓለም መድኃኒት ሙዳይ

የአዳም ዘር ሁሉ ሲሳይ

ነይ ነይ ማርያም ነይ ነይ

አምላክ ከሰማይ ያየሽ

የወገኖችሽ ክብር ነሽ

የአሕዛብ ሁሉ ድኅነት

ከአንቺ ተገኘ በእውነት

ክብርሽ ተገልጧል በልጅሽ

መንፈስ ቅዱስም ቀደሰሽ

የቃሉ ሕንፃ ሆነሻል

አብ ከሰማያት መርጦሻል

ፀሐይ ወጣልን ከእቅፍሽ

ሰማዕታት ሁሉ ከበቡሽ

ምክንያት ሆነሽ ሊድኑ

በልጅሽ ስራ ያመኑ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening