✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
አማናዊት ኪዳን
Lyrics
አማናዊት ኪዳን የሰው ልጆች ተስፋ
ድንግል ሆይ አማልጅን በሞት እንዳንጠፋ
የአባቶች ነቢያት ተስፋ ትንቢታቸው
የሐዋርያትም ጣዕመ ስብከታቸው
የሰማዕታት እናት የጻድቃን እመቤት
ደግሞም እኅታቸው ለሰማይ መላእክት
የነቅዱስ ኤፍሬም ድንቅ ድርሰታቸው
የነቅዱስ ያሬድ ድጓ ዝማሬያቸው
የእምነታቸው ቅመም አንቺ ነሽ በእውነቱ
የአባ ጊዮርጊስም ጸሎተ ሰዓታቱ
የአባ ሕርያቆስ ምሥጢረ ቅዳሴ
የመነኮሳት ስንቅ የኤፍሬም ውዳሴ
የሊቃውንት አበው የምስጢር ቋንቋቸው
የደናግል ተስፋ የጽድቅ አክሊላቸው
ሁኝልን መመኪያ በሞት እንዳንሰጋ
በዚች ዓለም ፈቃድ ከቶ እንዳንወጋ
ስለሌለን ተስፋ በዚህ ዓለም ስንኖር
አስታርቂን እመ አምላክ ከቸሩ ልጅሽ ጋር
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.