✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
አዛኝ እናታችን
Lyrics
አዛኝ እናታችን ቤዛዊተ ኩሉ
ስሟን ለሚጠሩ አድኚን ለሚሉ
የምሕረት አማላጅ ፈጣኗ ደመና
አይዞህ ልጄ አለችኝ ርህርህት ናትና/2/
ልቤ እያመነታ በቀቢጸ ተስፋ
መከራ ጸንቶብኝ ፈጽሞ ሳልጠፋ
ድንግል ብታነሳኝ እጆቿን ዘርግታ
በምልጃዋ ዳንኩኝ አገኘሁ ይቅርታ/2/
አባ ሕርያቆስ ይፈተን እውቀቱ
ምኑን ይቀድሣል ብለው ሲዘብቱ
በምስጋና ምስጢር ልቡን የቃኘችው
በብርሀን ጸዳል ቤቴን አበራችው /2/
የልቤን የውስጤን መናገር ፈርቼ
ዝም ባልኩኝ ጊዜ አንገቴን ደፍቼ
ምስጢሬን ነግሬ ስማፀን በደጇ
ለክብር አበቃችኝ አማልዳ ከልጇ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.