✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ማርያም ኀዘነ ልቡና
Lyrics
ማርያም ኀዘነ ልቡና ታቀልል /2/
ኀዘነ ልቡና /4/ ኀዘነ ልቡና ታቀልል /2/
ሕይወታችን አንቺን ባየች ቁጥር ትፈካለች ብሩህ ፋና
የመዳን መሰላል ዓርማችን ላዘኑ መጽናኛ
ለደከሙ ብርታት /2/ ከአንቺ ተገኘልን ዘለዓለም ሕይወት
ርስትሽን ኢትዮጵያን አስቢያት በጸሎት ታለቅሳለች ሰላምን ብታጣ
ሳትታክት ባንቺ መታመኗ ስምሽን መጥራቷ /2/ ስለሆንሽላት ነው ረዳቷ
ማርያም የልቡናን ኀዘን ታቀላለች
የልብን ኀዘን /2/ ታቀላለች
ብንከፋ በአማላጅነትሽ ተጽናናን ከጥላሽ ስር
ሰላምና ፍቅርን አገኘን
ጽድቅን የተጠሙ የተራቡ ሁሉ /2/ በስምሽ ተማጽነው ይረካሉ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.