✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
የዓለም ንግሥት የሆንሽው
Lyrics
የዓለም ንግሥት የሆንሽው ድንግል ማርያም እናቴ
ታመስግንሽ አንቺን ሁልጊዜ ሕይወቴ
ማርያም ባርኪኝ እመቤቴ እሰግድ ለኪ
እንዳልንገላታ ጠብቂኝ በኃጢአት ዓለም ጎዳና
ደግሞም እንድመገብ ሰማያዊ መና
ማርያም የአዳም ጤና እሰግድ ለኪ
ተሸጬ ስኖር ልጅሽ በኃጢአት ዓለም ከተማ
የሚያወጣኝ ጠፍቶ የእናት ልጅ ወንድም
ወጣሁኝ በልጅሽ ደም እሰግድ ለኪ
የአንቺ መንገላታት ሁል ጊዜ ያሳዝነኛል ሲወራ
በግብጽ በረሃ ያየሽው መከራ
ማርያም ነፍሴን አደራ እሰግድ ለኪ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.