✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
እናታችን ጽዮን
Lyrics
እናታችን ጽዮን እንላለን እኛ /2/
ስለወለድሽልን የሰላሙን ዳኛ
በሔዋን ምክንያት ቤታችን ተዘግቶ
ስንባዝን በሲዖል ሰላማችን ጠፍቶ
በቃለ ነቢያት ተስፋውን አናግሮ
አብሳሪውን ላከ ውበትሽን አፍቅሮ
መልአኩ ሲነግርሽ የሰላሙን ዜና
ንጉሥ መማረኩን በአንቺ ቅድስና
እንደቃልህ ይሁን ብለሽ ስትረቺ
ሰማያዊ ንጉሥ ተዋሐደ በአንቺ
የሕብስት ማደሪያ ጸዋሪተ ፍሬ
እንዳመሰገነሽ ዳዊት በዝማሬ
ኤልሳቤጥ ዘመድሽ ልዕልናሽን አይታ
ብጽዕት አለችሽ አደግድጋ ታጥቃ
ከእሳት ባሕር ጥሎን የሲዖል ዳኛ
ከሠራዊቱ ጋር ሲዘባበት በእኛ
መሲሑ ልጅሽ በበረት ተወልዶ
ከግዞት አወጣን ራሱን አዋርዶ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.