✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ኦ ድንግል ደስ ይበልሽ
Lyrics
ኦ ድንግል ደስ ይበልሽ
ኦ ቅድስት ደስ ይበልሽ
ገብርኤል በቃሉ ደስታን ያሰማሽ
ኦ ንጽሕት ደስ ይበልሽ
የዘለዓለም አምላክ እናት ስለሆንሽ
ኦ ንጽሕት ደስ ይበልሽ
ከፍጡራን ሁሉ በላይ ስለሆንሽ
ኦ ንጽሕት ደስ ይበልሽ
የነገሥታት ንጉሥ ዙፋን ስለሆንሽ
ኦ ንጽሕት ደስ ይበልሽ
የድኅነቴ ዓርማ ልዩ ምልክቴ
ለእኔም ነሽ እናቴ እመቤቴ /2/
የድኅነቴ ዓርማ ልዩ ምልክቴ
ልዩ ነሽ እናቴ እመቤቴ
የምታማልጅን ከቸሩ አባታችን
ለእኛም እናታችን እመቤታችን /2/
የምታማልጅን ከቸሩ አምላካችን
ለእኛም እናታችን አስታራቂያችን
ስለውድ ሀገርሽ ስለ ኢትዮዽያ
ለልጅሽ አሳስቢ ብለሽ ሃሌ ሉያ
ድንግል ሆይ አሳስቢ ብለሽ ሃሌ ሉያ
ስለውድ ሀገርሽ ስለ ኢትዮዽያ
ለልጅሽ አሳስቢ ብለሽ ሃሌ ሉያ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.