✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ተፈታ ችግሬ
Lyrics
ምን ይሆን ውለታሽ ድንግል የምከፍልሽ /2/
ላንቺ በመንገሬ ተፈታ ችግሬ /2/
የደካሞች ምርኩዝ የኃጥኣን ተስፋ /2/
ፈጥነሽ ትደርሽያለሽ የሰው ልጅ ሲከፋ/2/
ምን በግዞት ቢሆን ጨለማ ቢወርሰው/2/
እንዳዘነ አይቀርም አንቺን የያዘ ሰው/2/
ድንግል ሆይ በምልጃሽ አስቢኝ አሁንም /2/
ደካማ ነኝና መሳሳቴ አይቀርም /2/
ቅዱሳን ስምሽን ምግባቸው አድርገው /2/
ይኖራሉ በአንቺ በሐሴት ጠግበው /2/
አትርሺኝ እመ አምላክ ቤዛዊተ ኵሉ/2/
ላንቺ ሰጥቻለሁ ሕይወቴን በሙሉ /2/
ውዳሴ ማርያምን አልነጥልም ከአፌ /2/
በእሱ አይቼዋለሁ ፈተናን ማለፌ /2/
የዘነጋሽ ሁሉ ሲቸገር ቢጠራሽ /2/
አትይውም ችላ አላውቀውም ብለሽ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.