✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
አዛኝቷ እመቤት
Lyrics
አዛኝቷ እመቤት አትርሺኝ
የፈጣሪዬ እናት አስታውሽኝ
በምሕረትሽ /3/ ተማለጅኝ
የመከራ ነፋስ አጠቃኝ
ሕይወቴ ዝላለች ደከመኝ
ከጥላሽ ስር /3/ አሳርፊኝ
ከጭንቀት ባሕር ውስጥ አድኚኝ
ፈጥኜ ሳልጠፋ አስጥይኝ
እመቤቴ /3/ ተመልከቺኝ
አምላኬን ለማየት አልችልም
ኃጢአቴ ብዙነው አይሆንም
ካልደገፍሽኝ /3/ እኔ አልድንም
ድንግል እመቤቴ እባክሽ
ከፈጣሪ አስታርቂኝ ከልጅሽ
ያላንቺ ማን /2/ ያላንቺ ማን አለኝ አስታዋሽ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.