የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

እመቤታችን ላንቺ

Lyrics

እመቤታችን ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል /2/

ከሴቶች ሁሉ /3/ ተመርጠሻል

እያረጋጓት የሠማይ መላእክት /2/

ቤተ መቅደስ ኖረች /3/ አሥራ ሁለት ዓመት

ሐርና ወርቁን እያስማማች ስትፈል/2/

በእርሷ ላይ አደረ /3/ አካላዊ ቃል

መንፈስ ቅዱስም እንዳልተለያት አውቆ

ሰገዳላት /3/ ዘካርያስ ታጥቆ

መንፈስ ቅዱስም እንዳልተለያት አውቃ/2/

ተሳለመቻት /3/ ኤልሳቤጥ ተደንቃ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening