የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

የብርሃን መውጫ

Lyrics

የብርሃን መውጫ የሕይወት መሰላል

የተነበየላት ነቢዩ ሕዝቅኤል /2/

የሰሎሞን አክሊል የአሮን በትር

ሆና የተገኘች የአምላክ ማኅደር /2/

የዳዊት መሰንቆ የጌዴዎን ጸምር

አፍርታልናለች ያለወንድ ዘር /2/

እስኪ እናመስግናት እንዲህ በማለት

ቅድስት እናታችን ስብሕት ወቡርክት

አንቀጸ ብርሃን ማዕራገ ሕይወት

አዘክሪ ድንግል ለልጅሽ በእውነት

በደኅና እንዲያደርሰን ለመጪው ዓመት /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening