✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ድንግልን ፍለጋ
Lyrics
እወርዳለሁ ቆላ እወጣለሁ ደጋ /2/
የጭንቅ አማላጄን ድንግልን ፍለጋ
ድንግልን /3/ ፍለጋ
አቀብ ቁልቁለቱን አይችልም ጉልበቴ/2/
ምርኩዜ ከሌለሽ ድንግል እመቤቴ /2/
አንቺ የኖኅ መርከብ የሕይወት መገኛ/2/
መንግሥተ ሰማያት መግቢያችን ነሽ ለእኛ /2/
አልጫውን ዓለም የሚያጣፍጠው /2/
ስምሽ ማርያም ነው /2/ የዓለም ሁሉ /2/
እንደ በደላችን እንዳይሆን ቅጣቱ /2/
አማልጅን ከልጅሽ ድንግል አዛኝቱ /2/
የእናት አማላጅ የልጅ ተማላጅ /2/
ፊት አያስመልስም ይሁን ይሁን እንጂ
ይሁን ይሁን /3/ እንጂ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.