✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ሰላም ላንቺ ይሁን
Lyrics
ሰላም ለአንቺ ይሁን ቅድስት እናትችን
የአዳም ልጆች ተስፋ የሰማይ ቤታችን /2/
ነቢዩ ሕዝቅኤል የተነበየልሽ
ከአዳም ዘር መካከል አምላክ የመረጠሽ
የሥላሴ ዙፋን የተዘረጋብሽ
ንጽሕት አዳራሽ ተስፋችን አንቺው ነሽ
ለሐና ለኢያቄም አንቺን ቢሰጣቸው
ሁሉን ቻይ የሆነው ቸሩ አምላካቸው
ወስደው አስረከቡሽ ከቤተ መቅደስ
ማደሪያ ልትሆኚ ለመንፈስ ቅዱስ
የሐና ፍሬዋ የኢያቄም ዘር
ባንቺ ተከፈተ የተዘጋው በር
ባንቺ ቅድስና ጸጋን አግኝተናል
በተሰጠሽ ኪዳን ሕይወትን ወርሰናል
በኅሊና አምላክ ቀድሞ የነበርሽ
ለተከዘው አዳም መፅናኛው የሆንሽ
ርግማን ደርሶባት ሔዋን ስታነባ
የብርሃን ጸዳል ሆንሽላት አበባ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.