የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ዕፀ ጳጦስ ዘሲና

Lyrics

ጳጦስ ዘሲና ማርያም

የኖኅ ድንቅ መርከብ ተስፋው የአዳም

አምላክ ያስቀረልን ንጽሕቷ የአዳም ዘር

እናወድስሻለን እንድናገኝ ባንቺ ክብር

ወርቅ ተጎናጽፈሽ በልዑል ቀኝ የምትቆሚ

ምሳሌ የሌለሽ አዛኝቷ እኛን ስሚ

የአቤል የዋህነት የሴት ቸርነት

የሴም ቡራኬው ነሽ የአብርሃም እንግድነት

የይስሐቅ መዓዛ የያዕቆብ መሰላል

የአሮን ካኅን ልብስ የወርቅ ጸናጽል

የሳሙኤል ሙዳይ የጌዴዎን ፀምር

የኢያሱ ሐውልት የአሮን በትር

የሰሎሞን አክሊል የአሚናዳብ ሠረገላ

የኤልሳዕ ማሰሮ የኃጥኣን ከለላ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening