የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ድንግል ሆይ

Lyrics

ወላዲተ አምላክ የሁሉ እመቤት

ለምኝልን ለእኛ ከልጅሽ ምሕረት

በአንቺ አማላጅነት በእርሱ ቸርነት

እንዲያወጣን ነጻ ከፍርድ ቅጣት

ድንግል ሆይ ለምኝልን /2/

በበደል ተዳክሞ ፈቃደ ነፍሳችን

በምድራዊ ምኞት ናውዞ ልቡናችን

ፍቅርና ትሕትና ጠፍቶ ከፊታችን

ለሞት እንዳይሰጠን ይህ ክፋ ሥራችን

የምስኪኖች ተስፋ የደካሞችም ኃይል

ጠውልገናልና ጥላ ሁኚን ድንግል

እምነት ጨምሪልን ልቡናችን ይጽና

እመአምላክ አብሪልን የመዳንን ፋና

ፍጹም እንዳናዝን እንዳናፍር ኃላ

ተነጥቀን እንዳንቀር ከዘለዓለም ተድላ

በፍቅርሽ መልሺን ከሲዖል ጎዳና

ድንግል መመኪያችን ተስፋችን ነሽና

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening