የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

በብርሃን ጸዳል

Lyrics

በብርሀን ጸዳል ተከባ እመቤቴ

በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ

የጽጌውን ዜማ ስዘምር በደስታ

በምስጋናሽ መጠን ሲሰማኝ እርካታ /2/

እንባዬ ሲቀዳ ናፍቆትሽ መስጦኝ

ከደስታዬ በላይ አንቺን ስላየሁኝ

ምኞቴ ተሳክቶ ፊትሽን አይቼው

የለሊቱ ሕልሜ የቀን ምኞቴ ነው /2/

እሩህሩህ ነሽና ይህ ሕልሜ ተሳክቶ

አመስግኜሽ ድንግል ህሊናዬ ረክቶ

ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ

አንቺን በማመስገነን ሕሊናዬ ይትጋ /2/

ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ

አንቺን በማመስገን ሕሊናዬ ይርካ

የምስጋናሽ ብዕር ብርሃንሽ ልሁን

ስምሽ ይጻፍብኝ በልዩ ህብር /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening