የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ስምሽን ቢጠሩ

Lyrics

ስምሽን ቢጠሩ የማትጠገቢ

ምስጋናሽ ይብዛልኝ ወደቤቴ ግቢ

ጻድቃን የወረሱሽ የእግዚአብሔር ከተማ

የምንዱባን ሠፈር የሞላብሽ ግርማ

ቡራኬሽ ይድረሰኝ እናቴ የፍቅርሽ

ነፍሴን ለምስጋና ላንች ላፍስልሽ

የዓለምን አርነት ጽህፈት ያለብሽ

የሕይወት ፊደሌ ጽድቅ የተማረኩብሽ

ቢያነቡሽ አታልቂ ምስጢርሽ የሰፋ

ስምሽ ማራኪ ነው ከልብ የማይጠፋ

በሰው ሀገር ስኖር ሰው ጠፍቶ ከጎኔ

ባልንጀራ ሁነሽ የሌሊት ብርሃኔ

ተስፋን አብዝተሽ ጥሜን አስታግሽው

በብዙ በረከት ጎጆዬን ሞላሽው

ፍጹም ሩህሩህ ነሽ ስምሽ ጣዕም ያለው

ሐዘኔ ሲበዛ በአንቺ እጽናናለሁ

የዓለም እርካታ የሰላም ውጥን ነሽ

ጊዜ ለጣለው ሰው አይጨክንም ልብሽ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening