✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
ሰዓሉለነ
Lyrics
ሰዓሉ ለነ ቅዱሳን መላእክት ሰአሉ ለነ ጻድቃን ሰማዕታት ኅበ አምላከ ምህረት ሰአሉ ለነ
ለምኑልን ቅዱሳን መላእክት /2/ ለምኑልን ፃድቃን ሰማዕታት ወደ አምላከ ምሕረት ለምኑልን
አንተ የመረጥከውን ማን ይከሳል ያፀደከውን ማን ይወቅሳል ለሚገባው ክብርን መስጠት ታዝዟል እና በመጻሕፍት ያከበርካቸውን ባሪያዎችህን እናከብራለን ቅዱሳንህን /2/
ሁሉ መዳን እንዲይዙ የሚላኩ የሚታዘዙ ሠርክ በፊትህ እየቆሙ ጥዑም ቅዳሴን እያሰሙ በምስጋናቸው የሚያከብሩህን እናከብራለን መላእክትህን /2/
ጤዛ ልሰው ዳዋ ጥሰው ዋዕይ ቁሩንም ታግሰው በየፍርክታው በየዱሩ ሌጦ ለብሰው እየዞሩ በፅናታቸው ያከበሩህን እናከብራለን ጻድቃንህን /2/
እንደሚታረዱ በጎች ሆነው አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተው ስለ ስምህ እየተጣሉ ከአንበሳ ጋር እየታገሉ በተጋድሏቸው ያከበሩህን እናከብራለን ሰማዕታትን /2/
ከሕያው ቃልህ እየጠቀሱ መናፍቃንን ድል የነሱ በገዛ ደምህ የዋጀሀትን ቤተ ክርስትያንን የጠበቋትን በሕይወታቸው ያስደሰቱህን እናከብራለን ሐዋርያትህን /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.