✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
በጽድቅ የሚያምኑብህ
Lyrics
በጽድቅ የሚያምኑብህ ቅዱሳን በሙሉ ካንተ ባገኙት ኃይል ሁሉን ያደርጋሉ
እስራኤልን መርቶ ሙሴ ከግብጽ ሲያወጣ ቢከታተላቸው ፈርዖንም በቁጣ ባሕሩን ከፍሎ ሙሴ ሕዝቡን አሻገረ ከሠራዊቱ ጋር ፈርዖን ሰጥሞ ቀረ
ጎልያድ ሲፎክር ተማምኖ በኃይሉ የሚገጥመው ጠፍቶ ሁሉም ፈርተው ሳሉ ብላቴናው ዳዊት ከእረኝነት መጥቶ በአንድ ጠጠር ጣለው በአምላኩ ስም ወጥቶ
የእግዚአብሔርን መንፈስ ደፍረው ሊያታልሉ ሐናንያና ሚስቱ በሐሰት ሲምሉ ልባቸውን አውቆ ጴጥሮስ ገሠጻቸው በሞት ተቀሰፉ አንድ ሆነ ቀብራቸው
ጳውሎስና ሲላስ በእስር ቤት ተጥለው ሲዘምሩ ሳለ መከራውን ችለው ተናወጠ ወሕኒው እስከ መሠረቱ በጸሎታቸው ኃይል ከእስራት ተፈቱ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.