✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
Lyrics
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ በአካለ ሥጋና በአካለ ነፍስ /2/ ያሉ ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ
የእግዚአብሔር አይኖቹ ጻድቃንን ከማየት ጆሮዎቹም አይርቁም እነርሱን ከመስማት
የጻድቅ ሰዎ ጸሎት ኃይልን ታደርጋለች በምልጃቸው እንመን አናመንታ በአንዳች
ጊዜያዊው ፈተና ሳያሰቅቃቸው እሳትና ስለት ሳያስፈራራቸው ሰማያዊው ተስፋ ስለሚታያቸው በመከራ ሁሉ ጸኑ በእምነታቸው
ኃጥኡ ነዌ እንኳን በሲዖል እያለ ስለወንድሞቹ ምሕረት ከለመነ እናንተማ ጻድቃን በገነት ያላችሁ ምንኛ ትረዱን አምነን ስንጠራችሁ
ቀዝቃዛ ውኃ እንኳን በጻድቅ ሰው ስም የሚያጠጣ ቢኖር ዋጋው አይጠፋም ብሎ እንዳስተማረን ጌታ በወንጌል አምነን እንፈጽመው ዋጋ ያሰጣል
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.