✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
ወይቤሎሙ ሑሩ
Lyrics
ወይቤሎሙ ሑሩ ወመሐሩ ለዘየአምን ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት /2/
በሕይወታችሁ ስበኩ በኑሮአችሁ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በዓለም ዙርያ አዳርሱ ሳትሰለቹ ደመና ጠቅሳችሁ እንደወፍ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት /2/
በኃጢአት ገመድ ተይዞ ለታሠረው በዓለም ጽልመት ለተዋጠው የእውነት መንገድ ብርሃኑ ለጠፋበት በሁለንተናው ፈንጥቁበት ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት /2/
የጽድቅ እንጀራ በማጣት ለተራበው የሕይወትን ውኃ ለተጠማው ቀቢፀ ተስፋ በልቡ ላደረበት የወንጌልን ማእድ አቅርቡለት ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት /2/
አርድዕተ ወንጌል ካህናት ሊቃውንት ለተልኡኮ የጠራችሁ ከእውነተኛ ምንጭ ከጌታ ከባዕሉ የሕይወትን ውኃ የጠጣችሁ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት /2/
ሁለንተናችሁ ይነበብ ፊደል ይሁን በትዕዛዙ ሄዳችሁ ሥራችሁ ይብራ በዓለም እንደሻማ በሕይወታችሁ ሰብካችሁ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት /2/
ወይቤሎሙ ሑሩ ወመሐሩ ለዘየአምን ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.