✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
ቅዱሳን ጻድቃን
Lyrics
ቅዱሳን ጻድቃን ነቢያት ሐዋርያት /2/ ይለመኑናል ይታደጉናል ያማልዱናል ያስታርቁናል /2/
የእግዚአብሔር ዓይኖቹ ከቅዱሳኖቹ የእግዚአብሔር ጆሮዎቹ ወደ ጻድቃኖቹ ሁልጊዜ ነውና ሳይለይ ከእነርሱ ጻድቃን ሰማዕታት ስለ እኛ ሲያለቅሱ
ቃል ኪዳን አላቸው ከመድኃኔ ዓለም መታሰቢያቸውም በረከት ነው ለዓለም የአምላክን ሰላም መንግሥቱን ወርሰዋል እኛን ለማማለድ በቀኙ ቆመዋል
ለማግኘት ከፈለግን የቅዱሳን ዋጋ ከልብም ከሻትን የጻድቃንን ጸጋ በወዳጆቹ ስም በቅዱሳን ሁላ ድሆችን እናስብ የተራበ እናብላ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.