✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
የሕይወትን መዝገብ
Lyrics
የሕይወትን መዝገብ ቃሉን ያስነበቡህ የተዋሕዶ አርበኞች ቅዱሳን ዋኖችህ የድካም ዋጋቸው የእምነታቸው ፍሬ ያማረ ነውና ምሰላቸው ዛሬ
ምሥጢሩ ምንድነው ድል የማድረጋቸው ለሰማያዊ ክብር ለአክሊል ያበቃቸው የሕይወታቸውን መዝገብ ግለጥና አንብበው መፍትሔ አለውና ገድላቸው የአበው
ድካም ሲበረታ በመንፈስ ስትዝል ዙሪያህን ሲከብህ የኃጢአት መዕበል ጽናት ትዕግስት አጥተህ እንዳትሰናከል በጾም ጸሎት በርታ አባቶችን ምሰል
ዓለም ኢያርኮ ቢፈትንህ ሥጋህ ዲያብሎስም ቢያሴር ከመንገድ ሊያርቅህ ልትወድቅ አትችልም ምን ቢያይል ፈተና ካሰብክ የጸኑትን የተዋሕዶ ፋና
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.