✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
በእውነት ሰማዕታት
Lyrics
በእውነት ሰማዕታት ምርጦችህ ሆኑ የዓለሙን መንግሥት ክብሩን ሁሉ ስለመነኑ ተመተሩ ተቆራረጡ ስለ ስምህ ብለው ያላቸውን ሁሉ እያጡ
ተቃጠሉ በሰይፍ አለቁ የሚመጣውን ክብር መንግሥትህን ስለናፈቁ ምድራዊውን መንግሥት ተትው ወደ የማያልፍው ክብር ተጓዙ ከዓለም ወጥተው
ወደ ተኩላዎች መንጋ ተላኩ ቃለ ወንጌልህን በአሕዛብ ምድር ሊሰብኩ ወደ ሽንጎ አሳለፋቸው በነገሥታቱ ፊት በአደባባይ ሊያሰጨንቋቸው
በዚያች ሰዓት ሳይሳቀቁ ለሚናገሩት ቃል ሳያስቡ ሳይጨነቁ ጰራቅሊጦስ አጽናኝ ነውና እስከመጨረሻው ለታገሰ በእምነት ለጸና
መከራውን እያስቻላቸው እግዚአብሔር የድልን ዘውድ አቀዳጃቸው
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.