✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
ሞት በሌለባት ምድር
Lyrics
የዓለሙን ክብር ተድላውን መንነው ለአንዲት ሃይማኖት ተቀብለው ሞተዋልና ስለስሙ ብለው /2/
ሞት በሌለባት ምድር በዚያች ይኖራሉ በማያልፍ ክብር ደምቀው ያበራሉ ቅዱሳኑ ወዳጆቹ ሁሉ
ከቶ ያልረገጣት የአመጻ እግር የሰው ዓይን ያላያት ሐዲሲቷ ምድር አወረሳቸው እግዚአብሔር /2/
አመጻኛ ትውልድ በእምነቱ ያልጸና ምንም አይገባባት ቢጎመጅ ቢቀና አምላክ ለተገፉት ሰቷታልና አምላክ ለቅዱሳን መርጧታልና
ሰለ ቅዱስ ስሙ ስለ ክብሩ ብለው መራራውን ሥቃይ ስላለፉ ችለው ሞት የሌለባት ምድር አወረሳቸው /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.