የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት

Saints, Righteous & Martyrs

የጻድቅ ሰው ጸሎት

Lyrics

የጻድቅ ሰው ጸሎት ያድናል /2/ የነፍስን ቁስል ይጠግናል /2/

የፍቅር እመቤት ቤዛዊተ ኵሉ ለሌጅሽ አሳስቢ በደላችን ሁሉ ስለቃልኪዳኑ የቃሉ መሐላ ልመናሽን ሰምቶ አይለንም ችላ

ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቁ አባታችን ረድኤት በረከትህ ይድረስ ለሁላችን አባ ተክለ ሃይማኖት መቁጠሪያህን አንሳ ለምን ለልጆችህ እንዳናይ አበሳ

የእግዚአብሔር ወዳጅ ገብረ ክርስቶስ ልመና ጸሎትህ መድኃኒት ለነፍስ ፍቅርህ አይለየን ቂርቆስ ሆይ አደራ ነፍሳችን እንድትድን ከሲዖል መከራ

ጸሎቷ ደረሰ የክርስቶስ ሰምራ የእግዚአብሔርን ልብ ያቺ ቅድስት እናት ሰማዕቷ አርሴማ ለምና አስገባችን ከጻድቃን ከተማ

አባ ሐብተ ማርያም የብርሃን አምሳል በጸሎት አትርሳን ወድቀን እንዳንዝል ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያት ሁላችሁ ዘወትር አይለየን ጸሎት ልመናችሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening