የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት

Saints, Righteous & Martyrs

ምስጋና ጀመረ

Lyrics

ምስጋና ጀመረ ብሎ ሃሌ ሉያ ማኅሌታይ ያሬድ ዘኢትዮጵያ ምስጋና ጀመረ ብሎ ሃሌ ሉያ

ይበል /2/ ኧኸ ይበል ሃሌ ሉያ ጥዑመ ልሳን ያሬድ /4/ ዘኢትዮጵያ

ብሉይን ከሐዲስ ሐዲስን ከብሉይ አስተባብሮ ቃኘው ያሬድ ማኅሌታይ ምሥጢር ተገልጾለት ከምድር እስከ ሰማይ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ምሥጢር እያስማማ ምስጋና ጀመረ በጽዮን ከተማ

ለቅድስት ሥላሴ በሦስት ዓይነት ዜማ በወርቅ ጽናጽል በብር ከበሮ ዜማው ሲንቆረቆር በሰው ልጆች ጆሮ የያሬድ ዝማሬ ያድሳል አእምሮ

ተዋሕዶ አቅርቢ ለአምላክ ምስጋና በዕዝራ መሰንቆ በዳዊት በገና ዜማውን ከያሬድ ተምረሻልና

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening