✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
ኦ ፍጡነ ረድኤት
Lyrics
ኦ ፍጡነ ረድኤት /2/ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሊቀ /ቅዱስ/ ሰማዕት ሰላም ላንተ ይሁን ፍጡነ ረድኤት
የልዳው ፀሐይ ፍጡነ ረድኤት በጨካኝ ንጉሥ ፊት ቆምክ አደባባይ ታማኝ አገልጋይ ነህ ፍጡነ ረድኤት ስቃይ ያልበገረህ ፍጡነ ረድኤት አክሊልን አገኘህ መከራን ታግሰህ /2/
የፈጣሪውን ስም ፍጡነ ረድኤት ስለመሰከረ ፍጡነ ረድኤት ጊዮርጊስ ሰማዕት በሰይፍ ተመተረ የስቃይ መሣሪያ ፍጡነ ረድኤት ያላዘናጋህ ፍጡነ ረድኤት መንፈሳዊ አርበኛ ጊዮርጊስ አንተ ነህ /2/
ለእምነቱ ተጋዳይ ፍጡነ ረድኤት ታማኝ ወታደር ፍጡነ ረድኤት ቢነገር አያልቅም የተሰጠህ ክብር ስቃይ ቢያደርሱብህ ፍጡነ ረድኤት በመታገስህ ፍጡነ ረድኤት ሲወሳ ይኖራል ዘለዓለም ስምህ /2/
ለሰማው ይደንቃል ፍጡነ ረድኤት የአንተ ሰማዕትነት ፍጡነ ረድኤት ምሳሌ ይሆናል ለሁሉ ፍጥረት ገድልህ ይናገራል ፍጡነ ረድኤት ክብር እንደተሰጠህ ፍጡነ ረድኤት ጊዜ የማይሽረው ምግባር ሃይማኖት /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.