የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት

Saints, Righteous & Martyrs

ሐዋርያው መነኩሴ

Lyrics

ሐዋርያው መነኩሴ የመረጡት ሥላሴ /2/ ዋስ ጠበቃ ሁናት ተክልዬ ለነፍሴ

ዳሞት ትናገረው የአንተን ሐዋርያነት የወንጌል ገበሬ የጣዖታት ጠላት ፀሎተኛው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት ክንፍን የተሸለምክ እንደ ሰማይ መልአክ/2/

ብራናው ሲገለጽ ገድለ ተክለሃይማኖት ከሰው ልጅ ልቦና ይወጣል አጋንንት የቅዳሴው ዕጣን ሲወጣ ከዋሻው ምድርን ይባርካል ጸሎተ ምህላው /2/

የኢትዮጵያን ምድር አረስከው በመስቀል ጭንጫው ፈራረሰ ተዘራበት ወንጌል ትላንት የዘራኸው ዛሬ ለእኛ ሆኗል አምላከ ተክልዬ ብለን ተማፅነናል /2/

ከሱራፌል ተርታ ቆመህ ስታጥን ሥሉስ ቅዱስ ብለህ ስታመሰግን ጸሎት ትሩፋትህ ትህትና ስግደትህ ጾምህ ከፍ አድርጐ ሰማይ አደረሰህ /2/

ዛፉ ሲመነገል አምላክ የተባለው መተለሚ ሲያፍር ትልቅ ሰው ነኝ ያለው የተክልዬ ጸሎት ብዙ ነው ምስጢሩ ስድስት ክንፍ አወጣ ቢቆረጥ አንድ እግሩ/2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening