የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት

Saints, Righteous & Martyrs

ተክለሃይማኖት ተክለአብ

Lyrics

ተክለሃይማኖት ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ አባታችን አማልደን አስታርቀን ከፈጣሪ ጋር ከአምላካችን

በሦስት ቀን ሥላሴን ያመሰገንክ ከጭንጫ ድንጋይ ላይ ውኃን ያፈለክ አባታችን ተክለሃይማኖት አማልደን በኃጢአት እንዳንሞት /2/

እንደ መላእክት ክንፍ የተሰጠህ ሰማዕት ነቢይ አንድም ካህን ነህ መምህራችን አዲስ ሐዋርያ አስተምረን የፍቅር ባለሙያ /2/

እንደ ሱራፌል በሰማይ ሲያጥን በምድር ላይ ረድዕ ሆኖ ማገልገሉን በተሰጠው ጸጋ ሲያስነሳ ሙታን

ክህነቱ ከአንተው ዘንድ ናት አባታችን ፍታን ከኃጢአት /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening