የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት

Saints, Righteous & Martyrs

ተክለሃይማኖት ፀሐይ

Lyrics

ተክለሃይማኖት ፀሐይ የኢትዮጵያ ሲሳይ ምዕራፈ ቅዱሳን /2/ በነፍስም በሥጋም አትርሳን

የቅዱሳን አርዕስት የዋሻው ብርሃን የጸሎት ባለቤት የነዳያን መድኅን ገና ሳትወለድ አምላክ የመረጠህ የድውያን ህመም ፈዋሹ አንተ ነህ /2/

ገና በሦስት ቀን በሕፃንነትህ ጌታን አወደሰው ቅዱስ አንደበትህ ቀድሞም እግዚአብሔር አስቦሃልና በወጣትነትህ ወጣህ ለምነና /2/

ሌትና ቀን ሳትመርጥ ክረምትና በጋ ስትጸልይ ውለህ ስትጸልይ ነጋ በመቆምህ ብዛት አንድ እግርህ ቢነሳ

ጸሎትህን ፈጸምክ ለሥጋህ ሳትሳሳ /2/

ምንኛ ድንቅ ነው ቅዱስ የአንተ ብርታት ሰባት ዓመት ሙሉ በአንድ እግርህ ጸሎት የዓለም ግሳንግሷ ሀብት ሳይስብህ

ለኢትዮጵያ ጸለይክ ቆመህ በአንድ እግርህ/2/

የሃይማኖት ተክል የኢትዮጵያ አባት ምህረትን ከአምላክ ለአገርህ አሰጣት እኛንም አግዘን ጽድቅን እንድንሠራ በተሰጠህ ፀጋ ጠብቀን አደራ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening