✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
ገድሉ ተአምራቱ
Lyrics
ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው የተዋህዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ አባ ተክለ ሀይማኖት ዘኢትዮጵያ
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፍር የታጠቀ ንጹህ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ የጸጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት ባለስድስት ክንፉ ጻድቁ የእኔ አባት እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
ከካህናት መካከል ህሩይ ነው ተክለ አብ መጣው ከገዳምህ ልሳለምህ ብዬ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት ወልድ ዋሕድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት ጥላህ ያረፈበት ሆንዋል ጸበል እምነት ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክለአብ ዛሬም እንደጥንቱ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.