✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
አባ አቡነ
Lyrics
አባ አቡነ አባ መምህርነ /2/ አባ ተክለ ሃይማኖት /2/
እም አእላፍ /2/ ኅሩይ እም አእላፍ ኅሩይ /2/
አምላክ የጠራህ ለታላቅ ክብር ተክለ ሃይማኖት ብጹዕ መምህር ሐዋርያ ነህ በዚች በምድር /2/ ጸሎት ምሕላህ በእውነት ተሰማ ክብርህ ታወቀ በላይ በራማ /2/
ደብረ ሊባኖስ ተቀደሰች በእጅ መስቀልህ ተባረከች /2/ ኤልሳዕ ልበልህ ቅዱስ ዮሐንስ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ ነህ ቅዱስ /2/
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ
ጸሎትህ ሆኖናል መድኃኒትና ፈውስ /2/ ዛሬም ስንጠራህ ቃል ኪዳንህን አምነን ጠለ በረከትህ ለሁላችን ይሁን /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.