የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት

Saints, Righteous & Martyrs

በኃይልና ጥበብ

Lyrics

በኃይልና ጥበብ ትልቆቹን ትቶ ንጉሥ አደረገው ደሀውን ቀብቶ በእረኝነት ሜዳ ልቡን መረመረው እንደ ልቡ ሆኖ ዳዊትን ቢያገኘው /2/ ምንም ታናሽ ቢሆን አካሉ ቢኮስስ የተገባ ነገር በእግዚአብሔር ፊት ሊነግስ የሰው ዓይን ያልሞላው ትንሽ ብላቴና አባት ሆኖ ነበር በእግዚአብሔር ሕሊና/2/ የጌታችን እናት ታላላቅ ቅዱሳን ይልቁን ጌታችን የሰው ልጆች መድኅን በዓለም ሊወለድ ከዳዊት በሥጋ

ተስፋ ተሰጥቶታል እንዲሁ በጸጋ እንዲሁ በጸጋ እንዲሁ በጸጋ

የዋህ ስለነበር ዳዊት በሕይወቱ

ከበሩ ሲገባ ፈላለት ዘይቱ ሳሙኤል አከክብሮ በእግዚአብሔር ፊት ቀባው

አምላኩ ቢወደው ታላቅ አደረገው /2/ የምሥጋና ሃብቱን ከንግሥና ጋራ

አጣምሮ ሰጥቶታል መልካም እንዲሰራ

ሌትና ቀን ሳይል ምስጋና ሲመገብ እየደረደረ መሰንቆ በገና /2/

ሌትና ቀን ሳይል ሲመገብ ምስጋና እየደረደረ መሰንቆ በገና

ራዕይ ተሰጥቶት ከላይ ከደመና

ድንግልን አሳየው አንገቱን ሲያቀና /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening