የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት

Saints, Righteous & Martyrs

ንዋይ ኅሩይ

Lyrics

መልእክተ ወንጌልን በደሙ የጻፈ ስቃዩን ታግሶ ችሎ ያሳለፈ

በረሃብ በግርፋት በግት አብዝቶ በገድል በትሩፋት ጠላትን ድል ነስቶ

ንዋይ ኅሩይ ነው ለዓለም ያበራ ሐዋርያው ጳውሎስ ለጽድቅ የተጠራ እንቅልፉን እያጣ ሌት ተቀን ሳይታክት የኋላውን ትቶ ተጓዘ ወደፊት

በድካም ተጠምዶ በገድል እያረሰ

ከደማስቆ እስከ ሮም ቃሉን አዳረሰ እውነት ለመናገር ከቶ ያላፈረ ሕዝብን ከአሕዛብ በአንድ ያስተባበረ አምላኩ እንዳይናቅ ከልቡ የተጋ ጸንቶ የተጓዘ ለምትበልጠው ጸጋ

በሮም አደባባይ ሰማዕት የሆነ የተዋሕዶ አርበኛ ለአምላኩ የታመነ በጣዕመ ስብከቱ ዓለምን አጣፍጦ አክሊል ተቀዳጀ ሳይታክት ሮጦ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening