✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
ቅዱሳን መስክሩ
Lyrics
ተአምሩን ያያችሁ ቅዱሳን መስክሩ ፍቅሩን ቸርነቱን ለዓለም ንገሩ /2/
በየዋሕ ልቡና ንጹሕ መስዋዕትን አቤል ግለጥልን ለጽድቅ መሞትን ኖኅም ተናገረው ለአንተ የታየህን ዛሬን ብቻ ትተህ ነገን ማሰብህን
ተናገር አብርሃም የአምላክን ሥራ እንዴት እንደነበር ያኔ ስትጠራ ልጅህን ያሠጠህ ፍቅሩን ግለጥልን በእምነት መታዘዝን ለእኛ አስተምረን
ግለጥልን ዮሴፍ እንዴት እንደነበር ፍትወትን ድል ነስቶ ለሃይማኖት ማደር ከራስ ተድላ ይልቅ ለወገን መሞትን አስተምረን ሙሴ ፍቅርና ጽናትን
ለጠላት መጸለይ በማድረግ ይቅርታ አሳይ እስጢፋኖስ የፍቅርን እውነታ በፈተና ብዛት እንዳናመነታ
ቂርቆስ ጽኑ በለን ልባችን ይበርታ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.