✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
ቅድስተ ቅዱሳን
Lyrics
ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ድንግል ማርያም ንጽሕተ ንጹሐን ማርያም ድንግል ማርያም ታማልዳለች ከልጇ ከመድኃኔ ዓለም /2/ ታማልዳለች /4/
ልጄ ሆይ ይቅር በል እያለች
አባቶቻችን ነቢያት ወሐዋርያት ጻድቃን ወሰማዕታት /2/
ያማልዳሉ በእውነት/2/ ያማልዳሉ /2/ ያማልዳሉ /4/
አምላክ ሆይ ይቅር በል እያሉ
ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሚካኤል ወገብርኤል ሩፋኤልና ፋኑኤል ሠራዊቶቻቸውም ሁሉ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት አፊኒን ራጉኤልና ሳቁኤል
ሠራዊቶቻቸውም ሁሉ ያማልዳሉ ከክፉም ይጠብቃሉ/2/
ያማልዳሉ /4/
ከክፉም ይጠብቃሉ
በዱር በገደል በበረሃ በዋሻም ያሉ/2/ ያማልዳሉ በእውነት ያማልዳሉ/2/
ያማልዳሉ /4/ አምላክ ሆይ ይቅር በል እያለ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.