የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት

Saints, Righteous & Martyrs

በስመ አብ

Lyrics

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ተግባረ ተክለ አን ብዕሴ ሞገስ /2/ ይነገር ይሰማ እስከ አጽናፍ ድረስ የሚሆን ነውና ለሕሙማን ፈውስ /2/

በቃል ኪዳኑ አምነሽ ለሰጠው ፈጣሪ ለምግባረ ሠናይ ነፍሴ ተጣጣሪ /2/

ጋሻና ጦር ይዞ ከማደን አራዊት የሰው ልጅ እንዲያድን ሥላሴ መረጡት 2 እግዚአ አጋእዝት ጸጋን የሚሰጡ

ተክለ ሃይማኖት ብለው ስሙንም ለወጡ /2/ በኪደተ እግሩ ኢትዮጵያን ቀድሶ መጣ ደብረ አስቦ በመንፈስ ገስግሶ /2/ እግሩ እንኳን ቢሰበር በመቆም ብዛት ለሰባት ዓመታት ጸና በጸሎት /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening