የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት

Saints, Righteous & Martyrs

በየ ገዳማቱ

Lyrics

በየገዳማቱ በየበረሃው ውስጥ ስለተሰደዱ ፍቅርህን በመምረጥ የዓለም ውዳቂ ምናምንቴ ሆነው ስለፍቅርህ ሲሉ ክብራቸውን ትተው እግዚአብሔር ሆይ ማረን እግዚአብሔር ሆይ ማረን /2/

የዓለም ውዳቂ ጉድፍ በተባሉት በምድር እየኖሩ በጽድቅ ሕይወት ባሉት ዓለምንና አምሮቷን ትተው በመነኑት እግዚአብሔር ሆይ ማረን

እግዚአብሔር ሆይ ማረን /2/.

ሕያዋን በሆኑት እስከ ዘለዓለም ከኢየሱስ ጋራ ሞተው በመስቀል ዓለም ዓለም በናቃቸው እነሱም በናቁት አምላክ ራራልን አትጨክን በእውነት /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening