✦
የቅዱሳን፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት የምስጋና መዝሙራት
•Saints, Righteous & Martyrs
ልቡና የሚመስጥ
Lyrics
ልቡና የሚመስጥ አጥንት አለምላሚ ምድራዊ አይደለም ምንጩ ሰማያዊ ሄደህ የሰማኸው ከመላእክት ከተማ ምንኛ ጥዑም ነው ያሬድ ያንተ ዜማ ከትንሽ አንስቶ እስከ ግዙፎቹ አምላክ እንደ ሠራው በሥነ ፍጥረቱ ያልነገርከው የለም በዜማ ድርሰትህ በመንፈስ ቅዱስ ቃል ነውና እውቀትህ
ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የሆነውን መገረፍ መሰቀል መሞት መነሣቱን እናስታውሰው ዘንድ አመልክተህ ጽፈህ አበረከትክልን ከዜማ አስማምተህ
ለፀሐይ እናቱ ለብርሃን መውጫ ለድንግል ማርያም ውዳሴ እንዲገባ በምልአት በስፋት በምሥጢር በአንክሮ ያቀረብከው ዜማ ዛሬም አለ ከብሮ
ጸጋ በረከትህ ይደር በሁላችን
ሊቀ ተዋሕዶ ያሬድ አባታችን
ጠፍተው እንዳንባክን ያንተን ዜማ ዐዋቂ
አምላክ ያስነሣልን ሊቃውንት ጠባቂ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.