✦
የቅድስት ቤተክርስቲያን የምስጋና መዝሙራት
•Holy Church
በደምህ ዋጅተህ
Lyrics
በደምህ ዋጅተህ ያፀናሀትን
ጠብቅልን ቤ/ክርስቲያንን
ጽዮንን ክበቧት ቅጥሮቿንም ዙሩ
ሲል ያመሠገናት ዳዊት በመዝሙሩ /2/
ወልድ ዋህድ ብሎ ጴጥሮስ ሲመሰክር
መሠረት ነህ ብለህ ሰጥተኸዋል ክብር /2/
እመሠርታለሁ ባንተ መሠረት
የሲኦል አበጋዝ አይችሉም ለማጥፋት/2/
የቅዱሳን አገር የአምላክ ማደሪያ
ምዕራገ ጸሎት የሐጢአት ማስተሥረያ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.