የቅድስት ቤተክርስቲያን የምስጋና መዝሙራት

Holy Church

ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ

Lyrics

ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ

የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ

የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ

የአምላካችንን ቤት አንተውም ከቶ

ሁሉንም በሁሉ የሚሞላ ጌታ

ሙሽራው የሆነች ቤቱ ተሰኝታ

በክብር በሞገስ በጸጋ ተሞልታ

ደምቃ ትኖራለች ለዓለም አብርታ /2/

ዲያብሎስ ቢጨርስ ቀስቶቹን በሙሉ

ወጥመድ ቢዘረጋ በጉዟችን ሁሉ

እንሻገራለን የአምላክን ስም ጠርተን

አንዳች አይነካንም እርሱን ተጠግተን /2/

በስሙ መሰብሰብ በስሙ መስራት

ስለ ስሙ መኖር ለስሙ መሞት

ጠላት ዲያብሎስን ምን ባያስደስት

ይህ ነው ክርስትና ይሄ ነው ሕይወት /2/

ከትውልድ ለትውልድ የምናስረክበው

ለልጅ ልጅ አውርሰን ደስ የምንሰኘው

አይደል ብርና ወርቅ አይደል ሌላ ሐብት

ሃይማኖታችን ነው የኛ ርስት ጉልት /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening