✦
የቅድስት ቤተክርስቲያን የምስጋና መዝሙራት
•Holy Church
በዐለት ላይ ነውና
Lyrics
በዐለት ላይ ነውና ያቆማት አጽንቶ
በደሙ ነውና የቀደሳት ዋጅቶ
ይጠብቃልና ጠባቂዋ ተግቶ
የገሀነም ደጆች አይችሏትም ከቶ /2/
መንጋዋን ሊበትን ተኩላው ቢበረታ
ማዕበሉ መርከቧን ፍጹም ቢያንገላታ
የተቃወሟትን ሁሉን ድል ነስታለች
ዛሬም እንደ ፀሐይ ይኸው ታበራለች
የቄርሎስ እናት ናት የዲዮስቆሮስ
የአኖሬዎስና የነፊልጶስ
የወለተ ጴጥሮስ የክርስቶስ ሠምራ
የጴጥሮስ እናት የነመስቀል ክብራ
ኑፋቄ ቢነሳ ክህደቱ ቢነፍስ
ዙሪያዋን ቢከባት ቅጥሯን ለማፍረስ
የጸና ነውና በደም ተመሥርቶ
ትረታለች/ላልቶ/ እንጂ አትረታም/ጠብቆ/ ከቶ
አዕላፍ መላእክት ዙሪያ ከበዋታል
አዕላፍ ቅዱሳን ይጸልዩላታል
እኛ የማናውቃቸው እርሱ የሚያውቃቸው
ለእርሷ የሚሰሩ እጅግ ብዙ ናቸው
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.